Ethiopians


                                        

 
This Page Dedicated to
 
THE STAR THAT SHINE FOREVER!
 
TILAHUN GESSESE  
 
 

የአሁኖቹን አላውቅም እንጂ እኛ ልጆች እያለን አወሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ የሚል ግጥም ነበረን ማን እንደገጠመው እሱ አንድዬ ነው የሚያወቀው

የግጥሙ ትክክለኝነት ግን አሁንም ደረስ ማንም ሊነቀንቀው ያልቻለው ነው።ምናልባትም ወደ ፊት ለብዙ ብዙ አመታቶች እንዲሁ ሆኖ የሚቀጥል ይመስለኛል።
ሙዚቃ ለመስማት ቴሌቭዥን (ድሮ ድሮ መስኮተ ምትሃት ነበር አሉ የሚባለው) ለማየት በቻለው እና አቅሙ በፈቀደው ሁሉ በዚህም ሆነ በዚያ የጥላሁንን ዘፈኖች ያላዬ ያለሰማ ያለ አይመስለኝም

በዚህም ወይም በዛ ደግሞ የልብ የልቡን የነገረው ፤ውስጡን የቆሰቆሰው፤ ወኔውን ደረቱን ያስሞላው፤ እንባውን አስቁዋጥሮ እልህ ውስጣ ያስገባው ፤ሌሊት በጨለማ ቀን በጠራራ ጸሃይ ፍቅሩን ያሳሰበው፤

በሰርጓ ቀን ከሙሽራው ጋር ብቻቸውን የሚደንሱትን እንደህልም ያሳያት፤ ልቡን በሀዘን ስብር ያረገውን ቤቱ ይቁጠረው።
ዛሬ ጥላሁን በመሃከላችን የለም ግን እርግጠኛ ነኝ ዛሬም ነገም ተነገወዲያም በ”የህይወቴ ህይወት” እንዳራለን፤
በ”አልቻልኩም ንጭንጭሽን አልቻልኩም” ልክ ልካችንን እንነጋገራለን፤
ፍቅር እንደ ጉንፋን በየጊዜው እያየዘ ሲያስቸግረን “ካንድም ሁለት ሶስቴን” እናንጎራጉራለን፤
የወደድነው ቢከዳን ቃሉን ቢያጠፋ “እኔ በበኩሌ እወድሽ ነበረ አደራ ያልኩሽ ቃል ምነው ተሰበረ”ን እናዜማለን፤
በቃ አልቆለታል አትድረሺብኝ አልፈልግሽም ብለን ከወሰንንም ለዛም መፍትሄ አለው “ፍቅር ለብቻዬን ትቼሻለሁ አትምጪ ይቅር አችክ አችከ እችክ ትቼሻለሁ አትምጪ ይቅር ዞር በይ ከፊቴ ዞር በይ”ን በጎርባጣ ድምጻችን አናወርደዋለን፤
ጠላት ቢመጣ ሃገር ብትጠቃ “ ኢ …ት…ዮ…ጵ…ያ… ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ እናት ሃገር ኢትዮጵያ “ብለን ደረታችንን ነፍተን ጦር ጋሻችንን እናነሳለን(የመቼው ነህ አላችሁ? ክላሽ መትረየሳችንን ሳይሻል አይቀርም)፤
ኦሮሚኛ ጆሮዋችንን ቢቆርጡን ለማንሰማው ላባችን ጠብ እሰኪል “አኑሲያዳን” እኩል እንለዋለን፤
ምን ቢደላን ፍቅር አጥተን ልባችን አላርፍ ሲለን “ምግብማ ሞልቷል አምላክ መቼ ነሳኝ የፍቅር ርሃብ ነው እንዲህ ያከሳኝ”ን በፉጨት እናስነካዋለን፤
ሃገር ወገን ሲከፋ ተፈጥሮ ፊት ሲያዞር ዝናብ ሲርቅ ቤት ተዘግቶ ስደት ሲመጣ እጆች ለምጽዋት ሲዘረጉ ልባችን”ዋይ ዋይ ዋይ ሲሉ የረሃብን ጉንፋን ሲስሉ እያዝንኩኝ ባየኔ አይቼ ምን ላድርግ አለፍኩዋቼው ትቼ በረሃብ ስቃይ ቸነፈር ግማሹ ጎኔ ሲቸገር ክው ብሎ ደርቆ አፋቸው የግዜር ውሃ ሲጠማቸው”ን በተሰበረ ልባችን አንባ ባቆረዘዘ አይናችን ውስጥ እናስታውሳለን።
ሁሉንም ጠቅሼ ለመጻፍ ብሞክር እዚችው የተቀመጥኩባት ወንበር ላይ ልከርም እንደምችል ስለማውቅ አልሞክረውም በደፈናው ያ ለአብዛኛዎቹ የሙዚቃ ሰዎች አርአያ የሆነው ፤ እሱን ለመሆን እሱ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ህልም የሆነው ፤ በሁሉም የማህበረሰባችን ጉዳዮች ከሌባ ጣት አስከ ሃገር ፍቅር፡ ከቀጠሮ እስከ ህይወት ውጣ ውረድ ፡ ከጃፓኑዋ አስከ ሞናሊዛ ፡ ከትንሽ እስከ ትልቁ ፡ በማይጠገብ ድምጹ ያቀርብልን የነበረው
አርቲስት ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ ሚያዚያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።
ጥላሁን ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ላደረገው አስተዋፅኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ከ ኢትዮጵያ የስነ-ጥበብ እና የብዙሃን መገናኛ ሽልማት የህይወት ሙሉ አስተዋፅኦ ሽልማት ተቀብሏል።
አድናቂዎቹ እና ወዳጆቹ መጽናናቱን ይስጣችሁ።

   በጥላሁን መለየት አስተያየት ለመስጠት እዚህ ይጫኑ።

 

       

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ከጥላሁን ገሠሠ ዘፈኖች ጥቂቶቹ

Some of Tilahun's works

 

 ከጥላሁን ዜማዎች በጥቂቱ 


.

 

አዘነ ...አብነት ግርማ

 

የጥላሁንን መለዬት በተመለከተ በኤርትራ ቲቪ የቀረበ

A Special Report on Tilahun Loss in Eritrean TV.

 

 

 

 

 

 

*******ጥላሁን*******

ኧረ ስሙኝ ሰወች አንድ ጥያቄ አለኝ:

ምነው ባገር ሰላም ጸሃይ በረታብኝ::
ጉድለቱ ተሰማኝ ሆዴን ባር ባር አለኝ:
መከታ "ጥላየ" ሄደብኝ መሰለኝ::
ይብላኝ እንጅ ለሷ ለልጁ ሙዚቃ:
በድምጹ ተዉባ በትንፋሹ ደምቃ:
ለኖረችው ካዘን ራሷን አርቃ::
ጥልሽማ ሄደ ወደማይቀረው...
.....ግን ራሱ እንዳለው.....
" ሞት እንኳን ጨክኖ ወስዶ ከሚያስቀረው:
ምናለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው::"

አምላኬ ድጋፌ::
ሜሪላንድ, ዩ.ኤስ.ኤ

 


 

አኑርልን ገነት!

      የ ሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ፣

ጥ ሎን ኮበለለ እንባ እያፋሰሰ

      ላ ናየው ላያየን አመለጠን ድንገት፣

     ሁ ሉን እርግፍ አርጎ በፋሲካ ሌሊት

    ን ብረትና ሀብቱ ህዝብ ነበር ለሱ፣

ገ ንዘብና ጌጡ መከዳ ትራሱ

          ሰ ናይ ምግባር ይዞ አብሮን እንዳልኖረ፣

        ሰ ው መሆን ከንቱ ነው ጥሎን ተሰወረ

    ን ገሩ ለሁሉም የንጉሡን መራቅ፣

      ነ ገ ዛሬ አትበሉ ሀገር ህዝቡ ይወቅ

  ፍ ለጋ አይወጣ ከኡኡታ በቀር፣

        ስ መ ጥሩው ዘፋኝ አመለጠ ከምድር

     ይ ወደስ ይደነቅ ታምረኛ ድምፁ፣

  ማ ራኪ ቁመናው አይነግቡ ገጹ

       ር ቱዕ አንደበቱ ታጥቷል እንደዘበት፣

       ል ዑል አምላካችን የዓለም ባለቤት፣

    ን ጉሥ ጥላሁንን አኑርልን ገነት!


ማትያስ ከተማ ( welelaye2@yahoo.com )
ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም.
(April 20, 2009)

source ethiopiazare.com

 


 

 

 

 To make a Comment on Thlahun loss please click here.

 
Don't lose this site
Click here to bookmark Ethiopians

 

Welcome

Recent Photos

 

Featured Products

No featured products

Create a free website at Webs.com